top of page

ሳላወርስ አላልፍም

Updated: Apr 14

በመላኩ ተሰማ


ከጠዋቱ 3 ሰዓት ገደማ ሊሆን ይችላል፣ "መላኩ ተሰማ፤ ና አንተ" 'አናርኪስት' ውጣ!" የሚልና እንደቢንቢ/የወባ ትንኝም ያቃጭልብኛልና የቀፈፈኝ የካሳሁን መሆኑን የለየሁት ድምጽ አንባረቀ። እኔ ጆሮዬ ያዳምጥ እንጂ አንደበቴን መክፈት የሚያስችል አቅሙም/ፍላጎቱም ስላልነበረኝ ስለእኔ ሆነው ሁለት ወይም ሦስት ያህል እስረኞች በአንድ ድምጽ፣ "መላኩ መቆምም ሆነ መራመድ አይችልም"፤ ሲሉ መለሱለት።
ተሸክመው እንዲያወጡ ታዘዙና (ለገራፊ/ገዳይ አሳልፈው ስለማይሰጡኝ እነዚያው ጓዶች ወይም ሌሎች መልካም ሰዎች አይመስሉኝም) ፤ ሁለት-ሦስት ሰዎች ሆነው ከበሩ አውጥተው ውጭ አስቀመጡኝ። አልነሳ ስልለትም ካሳሁን ወደ አጥሩ ሄዶና አጣና ሰብሮም በመምጣት የተጫነችው ከብዷት መነሳት እንዳልቻለች ነገር ግን አለመጠች ተብላ እንደምትቀጠቀጥ አህያ ጀርባዬን እና ግራ ጎኔን መዠለጥ ጀመረ። ኋላ እንደታየው የግራ ኩላሊቴ ላይ ለቀዶ-ጥገና ያበቃኝ አደጋ በዚያው ጊዜ ዱላ ደርሶብኛል የሚል ግምት አለኝ። ታዲያ ይህ እየሆነ እያለ በዚያችው ሰዓትና ደቂቃ ውስጥ ደግሞ በስተቀኝና በሩ አጠገብ መሣሪያ ይዞ ከተቀመጠው ዘብ ጋር ዓይኖቻችን ተገጣጠሙ። ፊቱ ላይ ይታይ የነበረውን ሐዘንና በካሳሁን ላይ ያሳይ የነበረውንም ጥላቻና ንቀት መቼም ቢሆን አልረሣውም። ማንም ሆንክ ማን፤ ተራና ለወገን መከራ ያዘንክ ጭቁን ወታደር ነህና በህይወት ካለህና ይህንን ታሪክ የምታስታውስና የምታነበውም ከሆነ ከልብ አመሠግናለሁ ምስኪኑ ወገኔ!


ሦስተኛ/አራተኛ ሊደግመኝ ሲሞክር፤ በእልህ ጭምር ነው መሰል፤ ብድግ አልኩ። በኋላ በእስረኞቹ በአንዱ እንደተነገረኝም፤ "ፈገግ እይልክና በካሣሁንም ላይ በትዝብት ራስህን እያነቃነቅህ ነበር የተነሳኸው" ፤ የሚለውንና ተፈጠረ ተብሎ የተነገረኝን ምልክታዊ ተራክቦ ላስታውሰው ግን አልቻልኩም። ድርጊቱ በደመ-ነፍስ ጉዳይ መሆኑ ነው። እንደተለመደው በዋዜማው ምሽት ወደ " ማረፊያ ቤቱ " ሲያመጣኝ የነበረው ሁኔታ አሁን ግን ወደ ግርፍ ቦታው ልሄድለት አቅም ስለተሳነኝ እየቀጠቀጠና ማታ እንዳደረገው፤ እንደሞተ ውሻ እየጎተተም ቢሆን፤ ምርመራ ክፍሉ አደረሰኝ። በማረፊያ ቤቱና በመተልተያ/ምርመራ ክፍሉ መካከል በግምት በ40-50 ሜትር የሚደርስ ርቀትም ያለ ይመስለኛል።


ሳላወርስ አላልፍም በመላኩ ተሰማ

ከመጽሐፉ የተወሰደ ገፅ 140


Recent Posts

See All

ኦሮማይ

ከደራሲ በአሉ ግርማ መጀመሪያ ታተመ አዲስ አበባ 1975 ዓ. ም. . . . ባሬስታው ከፊት መታጠቢያው ሣህን ሥር ያለውን የውሃ ቧንቧ መዘውር ሄዶ ጫን ሲለው . . . በኮንክሪት የተቀበረ መሰሎ ይታይ የነበረው ትልቅ...

Comments


bottom of page