top of page

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ

1922-1929

ስለ ሴቶች ተማሪ ቤት


ግርማዊት እቴጌ መነን በአዲስ አበባ የሰሩት የሴቶች ትምህርት ቤት ባለፈው ዓመት በሚያዚያ ወር ተከፍቶ ሥራውን ሲሰራ ከርሞ ነበር። በዚህም ዓመት የምረቃ በዓል እንዲደርግለት ስለ ታሰበ የትምህርትና የሥነ ጥበብ ሚኒስቴር ዋና ዳሬክተር አቶ ሣህሉ ፀዳሉ ለመሳፍንትና ለመኳንንት ለውጭ አገር ሚኒስትሮችና ለቆንስሎች ጥሪ አድርገው መስከረም 22 ቀን ከቀትር በኋላ በታላቅ ስነ ስርዓት ተመረቀ።

በዚህ ጊዜ ግርማዊ ንጉሠ ነገሥትና ግርማዊት እቴጌ ልዑል መርድ አዝማች አሰፋ ወሰን ከተማሪ ቤቱ ሲደርሱ አቶ ሣህሌ ፀዳሉና ዲሬክተሪቱ ማዳም ጋሪከዋ ተማሪዎቹን አሰልፈው በሰላምታ ተቀበሏቸው። ወዲያው ከተጠሩት እንግዶች ጋር በየክፍሉ እየዞሩ መኝታ ቤቱንና ትምህርት መስጫውን ተመልከተው ለምረቃው በዓል ወደ ተሰናዳው ስፍራ ገብተው ተቀመጡ። በዚህ ጊዜ ተማሪዎች በዲሬክተሪቱ እየተመሩ የኢትዮጵያን ሕዝብ መዝሙር ዘመሩ። ከዚህም ቀጥሎ አቶ ሣህሉ ፀዳሉ የበዓል መክረቻ አጭር ቃል ተናገሩና የሚከተለውን የግርማዊትን ዲስኩር ለጉባዔው አነበቡ።

ይህችን ዓለም አመላላሽና ማመላለሻ መሆኑዋን የምታውቁት ነው ትውልድ ያልፋል ትውልድም ይተርፋል ሁሉም እንዲሁ ተመላላሽ ስለ ሆነ ያልተደረገ ነገር አስበን ለማየት ብንፈልግ ለማግኘት እንዘገያለን።

ገጽ 129

Recent Posts

See All
bottom of page