ሰው
#ማርታ፟፟_ቀፀላ Martha Ketsela ሰው ማነው? _እላለሁ፣ እኔንም አያለሁ_ከኔ እጀምራለሁ፣ በአምሳል ሁሉም ሰው ነው! በመንቀሳቀሱ ሰው ነህ ከሚያሰኘው፣ በመልበስ፣ ማጌጡ _ ደምቆ ከሚታየው ፣ ማን ብዬ ልለየው _ ሰውን ከሌላ ሰው? ሰው መሆን ካለብን _ ከተግባር አኳያ፣ የሰው ምንነቱን _ ጠልቀን ብንረዳ፣ በአካል በቁመቱ _ በውበቱ ገጽታ፣ አይደለም ማንነት _ የሰው ልጅ መለኪያ።
የመሆን ግዴታው _መጠበቅ ያለበት፣ እኛነታችንን _ አውቀን ስንሰራበት፣ በቀለም በጎሳ _መብቱን ሳንነፍግበት፣ ለኔም እምመኘውን _ለሱም ሳስብለት፣ ደልቶኝ ተትረፍርፎ _ ለሱም ስቸርለት፣ ሲደሰት ደስታውን _ሳዝን ስቆምለት፣ ያ! ነው ሰው መሆኔ _ ሰውም የሚያሰኘኝ፣ አለበለዚያ ግን _ መባል እመርጣለሁ፣ ሰው አልባ _ ከንቱ ነኝ። ገጽ 34
#የትም_ብዞር የግጥም መድብል #ማርታ፟፟_ቀፀላ Martha Ketsela ሰአሊ ገጣሚና ሙዚቀኛ/ዘፋኝ/

Comments