በደራሲ መሰረት ክንፈ ሃይሌ by Meseret Kinfe Haile

እራበኝ... እራበኝ.. እራበኝ.....ትላለች አገሬ፤
ጠፍቶ የሚያቀምሳት ፤ ከብዙ አንድ ፍሬ።
እኔን ቢያቅተኝ ወደላይ አያለሁ ጠፍቶብኛ አባቴ፤
አመመኝ.. አመመኝ.. አመመኝ ፤ ስትለኝ እናቴ
ተ..ገ..ላ..በ..ጠ..ብ..ኝ ፤ ተንሰፍስፎ አንጀቴ።
የትነህ አምላክ ሆይ? አባቴ ሆይ የት ነህ?
ራብ የማታውቀው ፤ እናቴን ሲርባት
ተራቡ ነው እንጂ ......
ተራብኩ አልነበረም ፤ እሷን የሚጨንቃት።
ልጅ ማጉረስን እንጂ
መጉረስ የማታውቀው እናቴን ከራባት
እስዋ ከተጣራች ፤ እርቦኛል ብላ
የጣር ዘመን ላይ ነው ፤ ትውልዱ በሞላ።
የእናት ራብ ማለት ፤ ለአገር ውድቀት ነው
የእናት ራብ ማለት ፤
የመጨረሻው ጣር ፤ የትውልድ ሞት ነው።
ገጽ 69 የተወሰደ
Comments