top of page
Writer's pictureEthiopian Writers

ጃገማ ኬሎ የሕይወት ታሪክ የበጋው መብረቅ

Updated: Apr 21, 2022

ፍቅረ ማርቆስ ደስታ

ጃጋማ በግርማዊነታቸው ትእዛዝ በሱም ፍላጎት 1933 አመተ ምህረት በሻለቃ ማእረግ በሆለታ ገነት ጦር ትምሕርት ቤት ገብቶ የአዛዥንት ኮርስ በመውሰድ የምድር ጦር ስራዊትን በማቆቆምና በሃላፊነት በተለያይ እግረኛ ብርጌድ ውሰጥ ከሰሩ በኃላ በውጭ ሃገር የከፍተኛ አዛዥነት ኮርስ ከወሰዱና የስራ ልምድ ካካበቱ በሆላ፤በብርጋዴር ጀነራል ማእረግ የብሔራዊ ጦር አዛዥ፤ቀጠሎም በሜጀር ጀነራል ማእረግ በአዲሰ የተቆቆመውን 4ኛ ክፍለ ጦርን በአዛዥነት መርተዋል።በምድር ጦር ሰራዊት ውስጥ ባገልገሉባቸው የጦር ክፍሎች በአመራራቸውና በአስተዳደራቸው በሰራዊቱ በጣም የተከበሩና የተወደዱ በስፓርት ወዳድነታቸውም ብዙ ግዜ የጦር ሐይሎችን ስፓርት በሃላፊነት የመሩ ጀነራል መኮንን ነበሩ።



ጀነራል ጃጋማ በ1959አመተ ምሕረት በባሌ በነዋቆ ጉቱ መሪነት የተቀሰቀሰውን የገበሬዎች አመጽ በከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ግዜ የባሌ ጠቅላይ ግዛት አስተዳዳሪና የጦሩ የበላይ በመሆን ዘመቻውን በመምራት ዋቆ ጉቱ ከነተከታዮቹ እጁን እንዲሰጥ በማድረግና ለግርማዊነታቸውም በሞትና በእስራት መቅጣት ለችግሩ መፍትሄ እንደማይሆን በማስረዳት እንዲያውም በተወለደበትና በሸፈተበት ደሎ መና አውራጃ አስተዳዳሪ እንዲሆን በማማከር የባሌ ክፍለ ሐገር ሙሉ ለሙሉ ሰላማዊ እንድሆን ከማድረጋቸው በላይ በገናሌ ወንዝ ላይ ያሰሩት ድልድይ፤የዲንሾ ፓርክን በማጠርና በመከለል የመሰረቱ የሐገር ባለውለታ መኮንን ናቸው።


ሌፍተናት ጀነራል ጃጋማ ኬሎ ከአብዮት በኃላ በጡረታ ተገልለው ከሠራዊቱ ቢሰናበቱም፤ ወያኔ እስካፈረሰውና እስከ ሸጠው ድረስ ከደሞዛቸው 2 % እየተቀነሰ ካቋቋሙት መኮንኖች ክበብ አንድም ቀን ሳይለዩ በሚወዳቸውና በሚያከብሮቸው መኮንኖች (ጃክ) እንድተባሉ በፍቅርና በመወደድ የተከበሩና የታፈሩ፤ታላቅ የሰራዊቱ ድንቅና ብርቅ መመኪያ ጀነራል መኮንን ነበሩ!!!










614 views0 comments

Recent Posts

See All

Commentaires


bottom of page