top of page

አንጉዝ

ፀሐይ መልአኩ

1984 ዓ. ም. አዲስ አበባ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ታተመ

በአባቷና በወንድሞቿ የግፍ አሟሟት ምክንያት የአካልና የመንፈስ መከራ ወድቆባት ስትማቅቅ ቆይታ በአረጋሽና በቅድስት ጥረት አገግማ መንፈሷ ተጠናክሮ አካሏ ታድሶ በተወለደችበት መንደር ለነዋሪነት ስትመለስ በርካታው ጊዜዋ የሀዘንና የለቅሶ ነበር። ሆኖም ወስና የተጋፈጠችው ኑሮ በመሆኑና የሰውም አመለካከት ተስተካክሎ በመሃበራዊ ወጉና ሥርዓቱ ውስጥ ስለተቀበላት እየተረጋጋች ተቀላቀለች። ለመኖር እያቀደችም ለኑሮ ጉዳይ የሚገባትን ለማድረግ ተነሳሳች። የአረጋሽ የመንፈስ ድጋፍ የቅድስት የጎጆ መውጫ ገንዘብ ችሮታ ጅምሯን አላጨለመባትም።

ከመፅሃፉ የተቀነጨበ

bottom of page